Episode Summary

ወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) ለሶስት ዓመታት ከማኅፀን ካንሰር ጋር ያካሔዱት ፍልሚያ አክትሞ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተለይተዋል። ባለቤታቸው አቶ አብርሃም ተዘራ፣ የቤተሰባቸው ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ እና የንስሃ አባታቸው መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ችሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል አስተዳዳሪ፤ የወ/ሮ ወርቅነሽን የሕይወት ዘመን አንስተው፤ ጥልቅ ሐዘናቸውን በመግለፅ ይዘክራሉ። የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ማርች 28 ቀን 2026 / መጋቢት 19 ቀን 2018 በወረቢ ቤተ መቃብር Corner Cemetery Rd & Railway Avenue 10:00 am ይፈፀማል።
... Show More

    No results